Surveys should never ask for any sensitive or secure data. Do not provide passwords, credit card numbers, identification numbers, or other sensitive information. Report Abuse.
Skip survey header

Preview / Test View

This link is intended for testing purposes only. It is not recommended that you distribute this link.
Show Comments
Loading comments...
COMMENT MODE
0

የማህበረሰብ የዳሰሳ ጥናት

የቫንስ ፕሮፐርቲስ ፕሮጀክት/Vance Properties Project

** Haga clic en el icono circular en la esquina inferior del lado derecha de la pantalla para ver esta encuesta en otro idioma. **
** Нажмите на иконку с изображением круга, расположенную в нижнем углу экрана, для просмотра этого опроса на другом языке. ** 
** Nhấp vào biểu tượng hình tròn ở góc dưới cùng bên phải màn hình để xem khảo sát này bằng ngôn ngữ khác. ** 
** ይህን የዳሰሳ ጥናት በተለያዩ ቋንቋዎች ለማየት በስክሪኑ የታችኛው ቀኝ ጎን ላይ የሚገኘውን የክብ ምልክት ይጫኑ። ** 
** ኣብቲ ታሕቲ ዘሎ የማናይ ኩርናዕ እቲ እስክሪን ዘሎ ክቢ ምልክት ብምጥዋቅ እዚ ዳህሰሳዊ መጽናዕቲ ብካልእ ቋንቋ ተተርጒሙ ምርኣይ ይከኣል፡፡ **


ቫንስ ፕሮፐርቲ/Vance Property ማህበረሰቡን በብዙ መንገዶች ሊያገለግሉ የሚችሉ እድሎችን የያዘ በኢስት ካውንቲ ከሚገኙት ትላልቅ ቦታዎች መካከል አንዱ ነው። የቦታው የተወሰነ ክፍል ለወደፊት የካውንቲው የአገልግሎት ፍላጎቶች ጥቅም ላይ ይውላል፣ ሆኖም ካውንቲው በተጨማሪም ለማህበረሰቡ ጠቃሚ የሆኑ ተጨማሪ ጥቅማ ጥቅሞችን የማቅረብ ፍላጎት አለው። እነዚህ ጥቅማ ጥቅሞች የማህበረሰብ ማረፊያ ቦታ፣ ፓርኮችና ክፍት ቦታዎች፣ የመኖሪያ ቤት መስሪያ፣ ለንግድ ስራ የሚውሉ፣ ደህንነታቸው የተጠበቀ የእግረኛና የብስክሌት መንገዶች፣ እና ሌሎችም ሊሆኑ ይችላሉ። በቦታው ላይ የሚሰሩት እነዚህ ጥቅማ ጥቅሞች ምን ሊመስሉ እንደሚችሉ በተመለከተ የእርስዎን ሀሳቦች መስማት እንፈልጋለን!

ይህን 90 ጋሻ ቦታ በተመለከተ የእርስዎን የወደፊት ራዕይ ለማወቅ ያስችለን ዘንድ ይህን አጭር የዳሰሳ ጥናት ይሙሉ! የእርስዎ ግብረ መልስ የቦታውን ዲዛይኖች ቅርጽ ለማስያዝ የሚረዳን ከመሆኑም በተጨማሪ የፕሮጀክቱ ስራ እየተከናወነ በሚቀጥልበት ወቅት ግብረ መልስዎን የሚሰጡባቸው ተጨማሪ እድሎች ይኖራሉ። 

ቦታው በግሪሻም/ Gresham በምስራቅና ምዕራብ በ182ኛ እና በ190ኛ እና በስትራክ /Stark መካከል የሚገኝ ሲሆን በስተ ሰሜን እና ደቡብ መካከል አካፋይ መንገድ አለው። ቦታውን በባለቤትነት የሚያስተዳድረውና የሚያንቀሳቅሰው የመልትኖርማህ ካውንቲ/ Multnomah County ሲሆን በርካታ የመልትኖርማህ ካውንቲ/ Multnomah County ህንጻዎችና ቫንስ ፓርክ/ Vance Park በቦታው ላይ ይገኛሉ። የቦታውን ግማሽ ያክሉን ቦታ የሚይዘው ከብዙ አመታት በፊት የቁፋሮ ቦታ የነበረውና በአሁኑ ወቅት ያለ ስራ ያለው ቦታ ነው።
በዳሰሳ ጥናቱ መጨረሻ ላይ $20 የስጦታ ካርድ ለማግኘት የሚመርጡትን የሎተሪ ዕጣ ያስገቡ። እርስዎ የሚሰጡን መረጃ ሙሉ በሙሉ ለእጣው አላማዎች ጥቅም ላይ ከመዋል በስተቀር ለየትኞቹም ሌሎች አላማዎች ጥቅም ላይ አይውልም።

ማንኛውም አይነት ጥያቄ ወይም አስተያየት ካለዎ እባክዎ አይሪን ኪም/ Irene Kim (የፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ) ጋር irene@cascadia-partners.com 503.459.7023 ወይም አና ጎርደን/Anna Gordon (የተሳትፎ መሪ) ጋር annagordon@verdenw.org 541.513.9292 ግንኙነት ያድርጉ
Survey Software powered by SurveyGizmo
Survey Software
ኣማርኛ